ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባልደረቦች በመስማት የተሳናቸው ላይ የግዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ

ሰኔ 3 ቀን 2014 - የኢመየብማ ባልደረባ

ለአንዳንድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባልደረቦች በመስማት የተሳናቸው ሰዎች ላይ ያቶኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰኔ 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ተሰጠ።

25 የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባልደረቦች በመስማት የተሳናቸው ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሲከታተሉ

የሥልጠናው ተሳታፊዎች
(ፎቶ፡ ኢመየብማ)

የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር ከተለያዩ ክፍለከተሞች ለተመረጡ 25 የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባለት የአንድ ቀን የግንዛቤ ማስጨባጫ ሥልጠና ሰጠ። የሥልጠናው ዓላማ ፖሊስ የተሰጠውን የሕግ ማስከበር ኃላፊነት በሚወጣበት ወቅት በመስማት የተሳናቸው ዜጎች ላይ የሕግ ጥሰት እንዳይፈጸም ለመከላል ነው። በሥልጠናው ወቅት ከዚህ በፊት በፖሊስ ጥቃት የደረሰባቸው መስማት የተሳናቸው አባላት ተሞክሮአቸውን ያካፈሉ ሲሆን ተመሳሳይ ስህተቶች እንዳይደገሙ መወሰድ በሚገባው ጥንቃቄና እርምጃ ላይ ከፖሊሶቹ ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጓል። በሥልጠናው ላይ የተሳተፉ የፖሊስ አባላት ከሥልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ ከሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር ለመካፈልና በኮሚሽኑ ውስጥ ግንዛቤ ለማስፋት እንዲሁም በመስማት የተሳናቸው ላይ ጥቃት እንዳይደርስ የበኩላቸውን ለመወጣት ቃል ገብተዋል። ሥልጠናው ለፌደራል ፖሊሶችም የሚሰጥ ሲሆን ቀጣይነት እንዲኖረው ጥረት እየተደረገ ነው።

ለ25 የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባሎች የግንዛቤ ማስጨነጫ ሥልተኛ ሲካሄድ

ሥልጠና ሲካሄድ
ፎቶውን በትልቁ ለማየት ጠቅ ያድርጉት
(ፎቶ፡ ኢመየብማ)

ገጠመኝ ሲያካፍል

ገጠመኝ ሲያካፍል
ፎቶውን በትልቁ ለማየት ጠቅ ያድርጉት
(ፎቶ ኢመየብማ)