አቶ በላይ ተክሉ የዓለም መ.የ. ሳምንት 1992 ሲከበር ኢመየብማን ረዱ።

ሰኔ 17 ቀን 2009 - የኢመየብማ ባልደረባ

የ1992 ዓለም አቀፍ የመስማት የተሳናቸው ሳምንት ነፍሰሄር አቶ በላይ ተክሉ ባደረጉት ዕርዳታ በደመቀ ሁኔታ ተክብሮ ውሏል። አቶ በላይ ተክሉ ብዙ የሥራ እንቅስቃሴ በሚታይበት መርካቶ በተለይም ቅዱስ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አካባቢ በኬኮችና ጣፋጭ ምግቦች ንግድ በጣም የታወቁ ነበሩ።

እነዚህ ደስተኞች ጥንዶች ጥር 21 ቀን 1998 ዓ.ም. ጋብቻቸውን በፈጸሙበት ጊዜ ከአቶ በላይ ተክሉ የኬክ ንግድ ቤት
    የጋብቻ ኬክ ተበርክቶላቸው ነበር።

እነዚህ ደስተኞች ጥንዶች ጥር 21 ቀን 1998 ዓ.ም.
ጋብቻቸውን በፈጸሙበት ጊዜ ከአቶ በላይ ተክሉ የኬክ ንግድ ቤት
የጋብቻ ኬክ ተበርክቶላቸው ነበር።
(ፎቶውን በትልቁ ለማዬት ይጫኑት)
(ፎቶ፡ በተክለ ደርሶ)

የአቶ በላይ ተክሉ እርዳታ ልዩ የሚያደርገው ለማኅበራችን የገንዘብ ድጋፍ ከማድረጋቸውም በላይ መስማት የተሳናቸው አባሎቻችን የጋብቻ ሥነ-ሥርዓታቸውን ሲፈጽሙ የጋብቻ ኬክ በነፃ እንዲወስዱ መፍቀዳቸው ማስታወቃቸውን ነበር። በዚህ በጎ ችሮታ መሠረት አንዳንድ አባሎቻችን ተጠቃሚዎች ሆነዋል። እርዳታውን ለማግኘት ከማኅበራችን ጋብቻቸውን የሚያከብሩ መሆናቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ይዘው መሄድ በቂያቸው ነበር።

አንዳንድ የኢመየብማ አባሎችና ሃላፊዎች በ1992 ዓለም አቀፍ የመስማት የተሳናቸው ሳምንት
    በተከበረበት ጊዜ ከአቶ በላይ ተክሉ ጋር

አንዳንድ የኢመየብማ አባሎችና ሃላፊዎች
በ1992 ዓለም አቀፍ የመስማት የተሳናቸው ሳምንት
በተከበረበት ጊዜ ከአቶ በላይ ተክሉ ጋር
(ፎቶውን በትልቁ ለማዬት ይጫኑት)
(ፎቶ፡ ከኢመየብማ)

አቶ በላይ ተክሉ የማኅበራችንን የስብሰባ አዳራሽ ስብሰባና ትርኢት በሚደረግበት ጊዜ አባሎች እይታ ሳይከለል ለመከታተል እንዲችሉ መድርኩ ክፍ ብሎ እንዲሠራ ለማድረግ ሃሳብ ነበራቸው። በጣም የሚያሳዝነው ግን ሃሳባቸውን ተግባራሚ ከማድረጋቸው በፊት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

አቶ በላይ ተክሉ በሞት ቢለዩም ቤተሰባቸው የጋብቻ ኬክ ለመስማት የተሳናቸው ማበርከቱን ቀጥለውበታል። ማኅበራችን ዓለም አቀፍ የመስማት የተሳናቸው ሳምንት በሚያከብርበት ጊዜም ደረቅ ኬኮች እና የመሳሰሉትን በነፃ ለማኅበራችን ሲያበረክቱ ቆይተዋል። ይህ በጎ ተግባራቸው ለወደፊቱም እንደሚቀጥል ተስፋችን ነው።