ሚስተር ኮሊን አለን የዓለም መስማት የተሳናቸው ፈደሬሽን ኢመየብማን ጎበኙ።

ሰኔ 18 ቀን 2009 - የኢመየብማ ባልደረባ

የዓለም መስማት የተሳናቸው ፈደሬሽን (ዓመየፈ) ፕሬዚዳንት ሚስቴር ኮሊን አለን የካቲት 18 ቀን 2007 ዓ.ም ኢመየብማን ጎብኝተዋል። ዶ/ር ሊዛ ኮፒነን የፈዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳን እና ዋና ፀሐፊ በነበሩባቸው ጊዜያት ማኅበራችንን ጎብኝተው የነበሩ ቢሆኑም የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳን ማኅበራችንን ሲገበኝ ግን የሚስተር አለን ጉብኝት የመጀመሪያው ነው።

የዓለም መስማት የተሳናቸው ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ሚስተር ኮሊን አለን መጋቢት 17 ቀን 2007 ዓ.ም. ኢመየብማን ጎብኝተዋል።

የዓለም መስማት የተሳናቸው ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት
ሚስተር ኮሊን አለን መጋቢት 17 ቀን 2007 ዓ.ም.
ኢመየብማን ጎብኝተዋል።
(ፎቶ፡- ተክለ ደርሶ)

በጉብኝታቸው ጊዜ ከኢመየብማ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ጋር ተገኛኝተው ተነጋግረዋል። የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ባደረገላቸው ግብዣም አንድ አባል ከማኅበሩ መሥራቾች፣ አንድ አባል የቀድሞ የማኅበሩ ሊቀመንበር፣ አንድ የማኅበራችን አባል የሆነ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት እንዲሁም ሌሎች አባሎች ተገኝተዋል።

በተጨማሪም ሚስተር ኮሊን አለን በቆይታቸው ወቅት ከኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ማኅበረሰብ አባሎች ጋር ተገናኝተዋል።

በሚስተር ኮሊን አለን የማኅበራችን ጉብኝት ወቅት ሚስ ዴቢ ኢዩቴ ከኡጋንዳ አብረዋቸው ተገኝተዋል። ሚስ ኢዩቴ ከ2000 እስከ 2003 ዓ.ም ድረስ የዓለም መስማት የተሳናቸው ፌደሬሽን የሚሮ አባል በመሆን አገልግለዋል።